መርጃ

1

ይመዝገቡ/ይግቡ

በአዲስባይ ላይ ሲመዘገቡ እንደ ግለሰብ ወይም ድርጅት የመመዝገብ ምርጫ አለዎት።

ግለሰብ

እንደግለሰብ ለመመዝገብ፡- ይመዝገቡ በሚለው ቦታ (‘ሊንክ’) ላይ ይጫኑ ከዚያም እንደገና በመጣው የምርጫ ፎርም (‘ፍላይ አውት’) ላይ ከላይ ያለውን ግለሰብ የሚለውን ‘ሊንክ’ ይጫኑ። በዚህ ጊዜ አጭር እና ፈጣን የምዝገባ ፎርም እንዲሞሉ ይቀርብሎታል። ይህ ፎርም መሰረታዊ የአድራሻ መረጃዎችን ያካትታል። ወይም ከፈለጉ በሌሎች ማህበረሰባዊ ድህረገጾች መግቢያ መጠቀም ይችላሉ።በሚሞላው ፎርም ላይ የሚከተሉት የግድ መሞላት አለባቸው።

በሚሞላው ፎርም ላይ የሚከተሉት የግድ መሞላት አለባቸው።

 • ስም [ስምዎ እና የአባት ስምዎ]
 • የኢሜይል አድራሻዎ [የመገልገያ ስምዎ እና የይለፍ ቃልዎ]
 • ጠቃሚ፡ ተመዝግበው ከገቡ በኋላ በመረጃ ማደራጃዎ ሁሉኑም መረጃዎችን መሙላትዎን እርግጠኛ ይሁኑ።

  የአዲስባይ ነባር ‘አካውንት’ ካለዎት ከመመዝገቢያ በስተግራ ያለውን ‘ሊንክ’ ይጫኑት።

  ድርጅት

  እንደ ድርጅት መመዝገብ ግልጽ የሆነ የድርጅትዎን ስም፣ ምርት (ግልጋሎት) እና ጥሩ ገጽታ ለመግለጽ ያሰጥዎታል።

  እንደድርጅት ሲመዘገቡ፡- ይመዝገቡ ‘ሊንክን’ በመጫን ሲሆን እንደ ግለሰብ ተመሳሳይ ፎርም ያቀርብልዎታል። በተጨማሪም በአካውንትዎ የንግድ ስምዎንና ምልክትዎን ማካተት ያስችልዎታል።

  ጠቃሚ፡- ከተመዘገቡና ለገቡ በኋላ በመረጃ ማደራጃዎ ላይ የሚሞሉትን መረጃዎች ሁሉ በትክክል መሞላታቸውን ያረጋግጡ።

  ለመጀመርያ ጊዜ ሲመዘገቡ የኢሜይል ማረጋገጫ ከአዲስባይ ይደርስዎታል። እርስዎም በኢሜይልዎ የተላከውን ማረጋገጫ ከጎበኙ ወይም የተላከለዎን የማረጋገጫ ‘ሊንክ’ እንደተጫኑ ወዲያውኑ ወደ አዲስባይ አካውንትዎ ይወስድዎታል። ከዚያም ጀምሮ በአዲስባይ ላይ እቃዎቾን ማስገባት እንዲሁም ማስተካከል (ማደራጀት) ይችላሉ።

  2

  መረጃ ማደራጃ

  ስምዎን፣ ስልክዎን እና የይለፍ ቃልዎን ማስተካከል ሲፈልጉ ከቋንቋ ምርጫ በስተግራ በሚገኘው የሰላምታ ቦታ ላይ ወደታች ያዘቀዘቀውን የቀስት ምልክት በመጫን የመረጃ ማደራጃዎ ውስጥ መግባት ይችላሉ።

  የግለሰብ የመረጃ ማደራጃ

  መሰረታዊ የሆኑ የግል መረጃዎትን ለምሳሌ ያህል ስምዎን፣ የአባትዎን ስም፣ የኢሜይል አድራሻዎን እና የስልክ ቁጥርዎን መቀየር (ማስተካከል) ይችላሉ። ከማህበራዊ ድህረገጾች (‘ሶሻል ሎግኢን’) ውጭ የተመዘገቡ ከሆነ የይለፍ ቃልዎን መቀየር ይችላሉ።

  የድርጅት የመረጃ ማደራጃ

  በድርጅት ስም ከተመዘገቡ የድርጅትዎን ስም፣ ኢሜይል፣ ስልክ፣ ፋክስ፣ አድራሻ፣ የንግድ ምልክት፣ የይለፍ ቃል፣ ወዘተ መቀያየር ይችላሉ።

  ከይለፍ ቃል በስተቀር ሁሉም በድርጅትዎ ስም የገለጹዋቸው መረጃዎች በድርጅትዎ የውስጥ ገጽ ላይ ለደንበኛዎ ሙሉ በሙሉ የሚታዩ ናቸው።

  3

  ዕቃዎን ይጨምሩ

  ዕቃዎን ለመሸጥ ወይም ለማከራየት ከርእስ መግለጫ (‘ባር’) ላይ የተጻፈውን እቃ ይጨምሩ የሚለውን ይጫኑ።

  በተለያዩ ዘርፎች የተከፋፈለ የአደራደር ስርዓት አለ።

  1. ኤሌክትሮኒክስ
  2. ሞባይል
  3. መኪና
  4. ቤት
  5. የቤት ዕቃ

  የአመዘጋገብ ሁኔታው በተመቻቸ እና ተመሳሳይ ሁኔታ እንደቀረበላችሁ ሁሉ እናንተም የምትፈልጉትን ዘርፍ በመምረጥ መሙላት ትችላላችሁ። እንዲሁም በማንኛውም ጊዜ መቀያየር ማስተካከል ይቻላል።

  አንድ

  ማንኛውም ነገር በምታወጡበት ጊዜ ስምና የስልክ ቁጥር ትጠየቃላችሁ።

  ሁለት

  የሁሉም ዕቃዎች ፎርም የዕቃዎችን መረጃ (መግለጫ) እንደየመደቡ የተለያዩ የአሞላል መጠይቆች አስፈላጊ ሲሆኑ የተወሰኑት እንደየምርጫ ናቸው። ተጨማሪ መግለጫ ስለ ዕቃዎት ካለዎት በትንተና የመግለጫ ላይ ማስቀመጥ ይችላሉ። በብዛት የሚሸጡ ቢሆኑም በዋጋ ማስቀመጥ የሚችሉት የአንዱን ዋጋ ብቻ ነው።

  ለሽያጭ ወይም ኪራይ የዕቃዎትን ዋጋ በቁጥር ያስቀምጡ ለምሳሌ 500። ያስተውሉ የአዲስባይ የመገበያያ ገንዘብ ምልክት አያስፈልገውም። አዲስባይ ለጊዜው ግልጋሎት የሚሰጠው በብር ብቻ ነው።

  ዕቃዎን አዲስባይ ላይ ካስቀመጡ በኋላ ሁለት አማራጮች አለዎት። ቀጥታ ለእይታ ማቅረብ ወይም ለጊዜው አስቀምጠው ከእይታ ውጪ ማድረግ ይችላሉ።

  ሶስት

  ለበለጠ መረጃ (ገለጻ) የዕቃውን ፎቶ ግራፍ ማስገባት ይቻላል። ይህን ካላስገቡ አዲስባይ ቦታውን በራሱ ምልክት ይሞላዋል። እባክዎ ፎቶግራፍ በሚያስገቡበት ጊዜ እነኚህን የፎቶ ፎርማቶች ተጠቀሙ፡ jpeg, bmp እና png።

  አስፈላጊ፡ እባክዎ የአዲስባይን የአጠቃቀም ስምምነት እና መረጃ አያያዝ ማንበብዎን እና መቀበልዎን ዕቃ ከማውጣትዎ በፊት በተሰጥዎ የማረጋገጫ ቦታ ያረጋግጡ።

  የያዙት ዕቃ በአዲስባይ ዝርዝር ላይ ከሌለ ሌሎች በሚለው ካታጎሪ ያስቀምጡ።

  4

  ዕቃዎችን መመልከት

  አዲስባይ የዕቃዎችን ዝርዝር መርጃ ዘርፎች በስተግራ በኩል ያስቀመጠ ሲሆን፣ እነሱን በመንካት የተካተቱትን ዕቃዎች ማየት ይችላሉ። ከዚህ በተጨማሪ አዲስባይ የተሻለ የመፈለጊያ ዘዴ ያዘጋጀ ሲሆን እነሱም ከርዕስ ቦታ በታች ሁሉም፣ አዲስ በ24 ሰዓት፣ በ24 ሰዓት ውስጥ የተሻሻሉ የኪራይ፣ የሽያጭ፣ የግል፣ የድርጅት ፣ወዘተ የሚሉ ምርጫዎች የቀረበ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ የዋጋ እና የቀን መፈለጊያ ዘዴዎችን በእያንዳንዱ ዘርፍ አካቷል።

  በዚህ መልኩ ከፈለጉ፣ ካጠናቀሩ በኋላ የተጣራውን ብቻ ወዲያውኑ ያመጣልዎታል።

  5

  የዝርዝር እይታ

  የቀረቡትን ዕቃዎች ዝርዝር ሁኔታ ለማየት የፈለጉት ዕቃ ላይ በመጫን የዕቃውን ዝርዝር መግለጫ ማየት ይችላሉ። እንዲሁም ቀዳሚውንና ተከታዩን ለማየት እዚሁ እያሉ ከላይ በፊት እና በኋላ የሚያሳየውን ቀስት ይጫኑ።

  አዲስ

  በ24 ሰዓት ውስጥ የወጡ አዲስ ዕቃዎች አዲስ የሚል ምልክት በአረንጓዴ መደብ ላይ በዕቃው የበላይ ቀኝ ላይ ምልክት ይኖረዋል።

  የተሻሻለ

  በ24 ሰዓት የተሻሻሉ (የተስተካከሉ) ካሉ በዕቃው የበላይ ቀኝ ላይ በብርቱካናማ መደብ የተሻሻለ ይላል።

  የዕቃዎት ዝርዝር ገጽታ ማሳያ የዕቃዎን ሁኔታ ለማስተካከል፣ ያሉበትን ይዘት ለመጨመር ለመቀነስ፣ ከእይታ ውጪ ለማድረግ እና ቀጥታ ለማጥፋት ያስችሎታል።

  6

  የዕቃዎ ዝርዝር

  የዕቃዎት ዝርዝር ገጽታ ማሳያ የዕቃዎን ሁኔታ ለማስተካከል፣ ያሉበትን ይዘት ለመጨመር ለመቀነስ፣ ከእይታ ውጪ ለማድረግ እና ቀጥታ ለማጥፋት ያስችሎታል።

  የእቃዎን ዝርዝር ለመቆጣጠር (ለማስተካከል ወይም ለማደራጀት) ከሰንጠረዡ በላይ ያሉትን አራት ቦታዎች (‘በተኖች’) ይጠቀሙ።

  አትም

  ይህ ለገዢዎች (ጎብኚዎች፣ ደንበኞች እና ተመልካቾች) እይታ እንዲቀርብ ያስችላል።

  አታትም

  ዕቃዎች ከገዢዎች (ጎብኚዎች፣ ደንበኞች እና ተመልካቾች) እይታ ውጪ እንዲሆን ያደርጋል። እንዲሁም ዕቃዎ በዝርዝሮ ብቻ ላይ እንዲገኝ ያደርጋል።

  አጥፋ

  ዕቃዎ ከአዲስባይ ውጪ ማድረግ እንዲሁም ከእርስዎ እይታ ውጪ በአጠቃላይ ማጥፋት እና ድጋሚ አለማግኘት ያደርጋል።

  አዲስ

  በአሉበት ዘርፍ ስር አዲስ ዕቃዎች ለመጨመር ያስችላል።

  የአስተካክሉ ምልክት በአሉበት ዘርፍ ምልክቱ ያለበትን ዕቃ ለማስተካከል ያስችሎታል።

  7

  ቋንቋ

  ይህ አዲስባይ ለጊዜው በሚጠቀምበት (ባቀረበው) የቋንቋ ዝርዝር የመረጡትን የሚመችዎን ቋንቋ አማርኛ ወይም እንግሊዘኛ ለመጠቀም ያስችሎታል።

  የአጠቃቀምም ሆነ የአመዘጋገብ ችግር ካጋጠመሆ እንዲሁም አስተያየት ካለዎት እባክዎ መልእክ ይላኩልን ወይም ያሳውቁን።

  የአዲስባይ አባላት