የአጠቃቀም ስምምነት

በመጨረሻ የወጣበት ቀን፡ መስከረም 16/ 2005 ዓ.ም.

ወደ addisbuy.com (አዲስባይ) እንኳን ደህና መጣችው። የ addisbuy.com ድህረ ገጽን በሚጠቀሙበት ወቅት የሚከተሉትን የድርጅቱን የውስጥ ስምምነቶች፣ ሁኔታዎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች ባሉበት ሁኒታ ሆነ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተሻሽለው በሚ ቀርብበት ወቅት ለመተግበር የተስማሙ ሲሆን አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ድርጅቱ በማንኛዉም ወቅት አሻሽሎና መጨመር የሚገባቸው ነጥቦች አካቶ ሊያቀርቡ ይችላል።

ስፋት

የ addisbuy.com ድህረ ገጽን ለመገልገል የአባልነት ምዝገባ ከማከናወን በፊት ይህን የተጠቃሚ ስምምነት ውል እንዲሁም የተጠቃሚ ሚስጥራዊ የመረጃዎች አጠባበቅ ደንብን በማንበብ ሙሉ ለሙሉ የተቀበሉ ሲሆን ነው ። ይህንን የተጠቃሚዎች የአጠቃቀም ስርዓት(ደንብ) ስምምነት ውልን በሚቀበሉበት ወቅት ማንኛውንም አይነት ድርጅቱ የሚሰጣቸውን ግልጋሎቶችን ሆነ በድህረ ገጹ ላይ በሚገለገሉበት ወቅት፤ እንዲሁም ድርጅቱ በድህረ ገጹም ሆነ በሌላ መንገድ ለሚሰጣቸው ግልጋሎቶች ለመስጠት እንዲችል ያስቀመጣቸው ያስቀመጣቸውን አጋዥ መገልገያ መሳሪያዎችን በሚጠቀሙበት ጊዜ ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል።

አዲስባይን ሲጠቀሙ

የአዲስባይ ድህረገጽ ሆነ ግልጋሎቶችን እንዲሁም አጋዥ መገልገያ መሳርያዎችን በሚጠቀሙበት ወቅት መደረግ የሌለባቸው ነጥቦች እንደ እንደሚከተለው ተቀምጧል።

 1. በድህረ ገጹ ላይ የሚቀመጡ የመረጃ ይዘቶችን ሆነ የዕቃዎች ምስሎችን ተገቢ ባልሆነ የድህረ ገጽ ቦታ ላይ ማስቀመጥ፤
 2. ማንኛዉም አይነት ህግጋትን መተላለፍ፣ የሌላ ሶስተኛ ወገን መብት ወይም የድርጅቱን ፖሊሲ የሚጻረር ድርጊት መፈጸም ፤
 3. የዕቃዎች ዋጋ መቀያየር ወይም የሌላን ተጠቃሚ ዝርዝሮች ዉስጥ ጣልቃ መግባት፤
 4. በድህረገጹ ላይ ትክክለኛ ያልሆኑ፣ አሳሳሶች፣ ያልተረጋገጡ፣ የሀሰት፣ መረጃዎችን ማስቀመጥ (የግል መረጃዎችን ያካትታል)፤
 5. ማንያዉም አይነት የአስተያየትና የአሳብ መስጫ መንገዶችን የሚያቃልል ድርጊት ዉስጥ መገኘት (ለምሳሌ ለአዲስባይ የሚሰጡ አስተያየቶችን ከድህረገጹ ውጭ ወደሚገኝ ስፍራ ማሳየት፣ ማምጣትና መላክ ወይም ከድርጅቱ አላማ ጋር ተያያዥነት ለሌለው አላማ መጠቀም)፤
 6. የአዲስባይ መጠቀሚያ አካዉንትዎን ወደ ሌላ ማስተላለፍ፤
 7. አስፈላጊ ያልሆኑ ኢ-ሜይል መልክቶችን ማስተላለፍ ወይም ማሰራጨት እንዲሁም፤
 8. የኮምፒዉተር ቫይረሶችን ወይም የድርጅቱንም ሆነ የአዲስባይን ተጠቃሚ ደንቦችን ፍላጎትና ንብረቶች ላይ ጉዳት (እክል) ሊፈጠር የሚችል ማንኛውም የቴክኖሎጂ ዉጤት፤
 9. ከአዲስ ባይ ድህረገጽ፣ ግልጋሎት ወይም አጋዥ መገልገያ መሳርያዎችን ይዘት መገልበጥና ማሻሻል ማሰረራጨት ወይንም የአዲስባይን የቅጅ መብት የንግድ ምልክትን ተዛማጅነት ያላቸውን መብቶችን መጣስ፤
 10. ከተጠቃሚው ፍቃድ ዉጭ የግለሰብን የግል መረጃዎች መሰብሰብ (የኢ-ሜይል አድራሻዎችን ያካትታል)፤
 11. በድህረ ገጹ፡ ፖለቲካዊ ድርጊቶችን፣ የተከለከሉ ዕጾችን፣ ዘረኝነትን፣ የጦር መሳሪያዎችን ወዘተ በህግ የተከለከሉ ድርጊቶችን ማከናወን ወይም አገልጋሎት መጠቀም።

1. የአገልግሎቱ ጥቅም

ህጋዊ የሆነ የኮንትራት ዉል ለመዋዋል የሚያስችል ዕድሜ ላይ እንደሚገኙ ታሳቢ በማድረግ እንዲሁም ከማንኛውም ህጋዊ መብቶች በኢትዮጵያ ህግ መሰረትና በሌሎች ተግባራዊ በሚደረጉ ህግጋት መሰረት እገዳ ያልተጣለቦት ግለሰብ መሆኖን በማመን ይህንን አገልግሎት ይዘን የመጣን ሲሆን፤ግልጋሎቶቻንን በተገቢው መንገድ፣ ማገናኘት እንዲያስችሎት የተወሰኑ ወቅታዊ የሆኑ መለያ አድራሻ፣ ሊገኝበት የሚችሉበት አድራሻ እና ተዛማጅነት ያላቸውን መረጃዎችን ከምዝገባ ወቅት ጀምሮ የአዲስባይን ግልጋሎት እስከቀጠሉበት የሚጠየቁ ሲሆን ሚስጥራዊ (የይለፍ) አድራሻዎን ሚስጥራዊነት የመጠበቅ ግዴታና ሃላፊነት ያለቦት ሲሆን በእርሶ አድራሻ ለሚደረግ እንቅስቃሴ ሃላፊነት ይወስዳሉ፤ ማንኛዉም አይነት ሃላፊነት በሌለው አካል ሚስጥራዊ የይለፍ አድራሻዎ የደህንነት ጥሰት በሚደርስበት ወቅት ወዲያዉኑ ለአዲስ ባይ ለማሳወቅ የተስማሙ መሆኑን እያሳወቅን ሚስጥራዊ የይለፍ መክፈቻዎን ሚስጥራዊነት ካለመጠበቅ ሆነ በቃ የሆነ መረጃ ካለመስጠት የተነሳ ለሚፈጠር ማንኛውም አይነት ጥፋት አዲስ ባይ ሃላፊነቱን አይወስድም።

2. ተመጣጣኝ እርምጃዎች

ሁሉም አይነት የጽሁፍ መረጃዎች፣ ምስሎችና መልዕክቶች ወይም ሌሎች ይዘት ያላቸው መረጃዎች የሚቀርብሎት ያለው የመረጃ ይዘቱ ባለቤት በመሆን የሚያቀርበው ግለሰብ መሆኑን መገንዘብ አለቦት።ድርጅቱ የቅድመ ሳንሱር ፣ ማጣራት፣ አለመቀበል፣ ማሻሻል ወይም ማንኛውም በአዲስባይ ግልጋሎት ላይ የሚገኝ ይዘትን የማንቀሳቀስ ሙሉ መብቱ የተጠበቀ ቢሆንም ይህን ለማድረግ የተጣለበት ምንም አይነት ግዴታ ግን የለበትም። በመሆኑ አዲስባይን ግልጋሎት በሚጠቀሙበት ወቅት የተከለከሉ አጸያፊና ሊሚያበሳጩ የሚችሉ ይዘት ያላቸው መረጃዎች ሊያጋልጡ የሚችል ሲሆን ግልጋሎቱን የሚጠቀሙ እራሣቸው ሃላፊነት መሆኑንና አዲስባይም ሃላፊነቱን እንደማይወስድ ሊገነዘብ ይገባል።

አዲስባይን በመጠቀም የሚያስተላልፉት ወይም የሚያሳዩት የመረጃ ይዘት እንዲሁም ከዚህ በመነሳት ለሚሰጥሆ ለሚፈጠር ምንም አይነት ምላሽ ሙሉ በሙሉ ሃላፊነቱን ለመውሰድ ተስማምተዋል። የአዲስባይን ግልጋሎት ህጋዊ ለሆኑ ጉዳዮችና አግባብነት ባለው መንገድ ከአዲስባይ ደንቦች፣ መርሆችና፣ ስምምነቶች ጋር በማይጣረስ ሁኔታ ለመጠቀም ተስማምተዋል።

የአዲስባይን ግልጋሎት ጣላቃ በመግባት እና የመረጃ መረብ ግንኙነት እንዲቋረጥ በማድረግ እንቅስቃሴ ዉስጥ ላለመካፈል ተስማምተዋል።

ከድርጅቱ የመረጃ አጠቃቀም የግል መረጃ ደህንነት ደንቦች ከአዲስባይ ደንቦችና መርሆች ጋር በማስማማት ለመጠቀም ተስማምተዋል። ከኢትዮጲያ ዉጪ ለሚገኙ ተጠቃሚዎች በአጥቢያቸው በማንኛዉም የኢንተርኔት አጠቃቃቀም ህግጋት እንዲሁም ተቀባይነት ያላቸው ይዘቶችን ከኢትዮጵያና ወደ ኢትዮጵያ ወይም ከሃገራቸው ነዋሪዎች ጋር መረጃዎችን የሚመለከት ሁኔታ የተመለከተ ከተቀመጡ ህግጋቶች ጋር በማይጋጭ መንገድ ለማከናወን ተስማምተዋል።

3. የድርጅታችን የመረጃ አጠባበቅ

የድርጅታችን የመረጃ አጠባበቅ መንገድን በተመከከተ እባክዎን የድርጅታችንን privacy policy ይመልከቱ የአዲስባይን ግልጋሎቶችና በሚጠቀሙበት ወቅት አዲስባይን በአድራሻዎ የሚገኝ መረጃዎችን እንዲሁም በአድራሻዎ የሚገኝ ማንኛቸውም አይነት ይዘቶችን በህጋዊ አካላት ተፈላጊ ከሆነ መረጃዎችን አሳልፎ እንደሚሰጥ የተስማሙ ሲሆን አሊያም የመጠበቅ ወይም የማጋለጥ አስፈላጊና ምክንያታዊ የሚሆነው

ሀ) ባሉት ህግጋቶች መሰረት የሚተገበር ከሆነ እና የመንግስት ጥያቄ ከሆነ፣ለ) የህግ መተላለፍ በተመለከተ በዉሉ መሰረት ማስገደድና በቀጣይነትም ምርመራ ማካሄድ የአዲ ስባይ ግልጋሎ ት ስርጭትና የተክኒካዊ ሂደት የእርስሆን ያስቀመጡትን ይዘት ጨምሮ ሊገነዘቡት የሚገባ ሀ) በተለያዩ የመረጃ መረቦች ላይ ስርጭቱን ሊተላለፍ ይችላል፣ ለ) የመረጃ መረብን መሳሪያዎችን ወይም አገልግሎትለማግኘት የሚጠይቀው የቴክኒካል መስፈርቶች ሊለዋወጥ ይችላል፤

በተጨማሪም ሊገነዘቡት የሚገባ ነገር የእርስሆን domain administrator የእርስዎን አድራሻና የሚያስቀምጡትን የመረጃ ይዘት ማግኘት ጨምሮ ምንአልባትም እንዳይንቀሳቀስ ማድረግን ወይም ሙሉ ለሙሉ አድራሻዎን የመክፈትና የቀድሞ አድራሻዎን እንዳይጠቀሙ ማድረግ እንደሚችል ተስማምተዋል።

4. የአዲስባይ ሕጋዊ መብቶች

የአዲስባይ መብቶች

የአዲስባይ ግልጋሎቶች እንዲሁም ማንኛዉም አገልግሎቱን ለማግኘት አስፈላጊ የሆኑ ሶፍትዌሮች የባለቤትነት ይዞታና የኢንፎርሜሽን ምስጢራዊነት በአይምሮ ንብረት እንዲሁም በሌሎች ህግጋትና ስምምነቶች ጥበቃ እንደሚደረግላቸው አውቀው ተስማምተዋል።በተጨማሪም በእስፖንሰሮች የሚደረግ የማስተዋወቂያ ይዘት እንዲሁም በአዲስባይ አገልግሎት ስር ሲቀርብ የቅጅ መብት ፣ የንግድ ምልክት ፣ የአገልግሎት ምልክት፣ የፈጠራ መብት ወይም በሌላ የአይምሮ ንብረት ህግጋት ጥበቃ እንደሚደረግላቸው አውቀው ተስማምተዋል።ከአዲስባይ ስልጣን ካልተገለጸ በስተቀር ወይም በሌላ ሶስተኛ ወገን ባለቤትነት ካልተገለጸ በስተቀር እርሶ ላለማሻሻል፣ ላለማከራየት፣ ላለማከፋፈል ወይም በአዲስባይ ግልጋሎት ላይ የተመሰረተ ቀጣይ ስራ ከመፍጠር ወይም ሶፍትዌሮችን ሙሉ በሙሉ ወይም የተወሰነ ይዘቱን ማከናወን ከባለስልጣኑ ባለቤቱ የጽሁፍ ፍቃድ ስምምነት ዉጭ ላለማከናወን ተስማምተዋል።በዚህ ዉል መሰረት አዲስባይ እርስሆ የሚጠቀሙበት የግል ለማንም የማይተላለፍ ለሁሉም የተሰጠ ሶፍትዋሮችን የመጠቀም ፍቃድ እንደሰጦት ያረጋግጣል።ስለዚህ ለሌላ ሶስተኛ ወገን የማባዛት፣ የማሻሻል እንዲሁም በእኛ ተመሳሳይ የሚደረግ ሌላ ስራ ቀይሮ መስራት፣ ቀይሮ በመገጣጠም ወይም source code ለማግኘት ፣ ለመሸጥ፣ የደህንነት ዋስትና መስጠት ወይም በሶፍትዋሩ ላይ ያሎትን መብቶች ለሌላ ሶስተኛ ወገን ማስተላለፍ የማይቻል ሲሆን፡ ይህንማድረግ የሚቻለው በጽሁፍ አዲስ ባይን ወይም ሌላ ህጋዊ አካል ፍቃደኝነቱን ካረጋገጠ ብቻ እንደሆነ አውቀው ተስማምተዋል ።

የሶፍትዋሮችን ተሻሽሎ የቀረቡ ምዕራፎችን ላለመጠቀን የተስማሙ ሲሆን ይኸውም የአዲስባይን አገልግሎት ለማግኘት እንዲያስችል ስልጣኑ በሌላ አካል ተሻሽሎ የተሰራ ሶፍትዌርን ያካትታል። የአዲስባይን አገልግሎት በድህረገጹ አቀራረብ መልኩ መጠቀም ከዚህ ውጭ በጽሁፍ ስምምነት ካልተገለጸ በስተቀር የጸና ይሆናል።ከዚህም ባሻገር ላለማባዛት ፣ አስመስሎ ላለማቅረብ፣ ወይም ከሌላ የንግድ ምልክት የአገልግሎት ምልክት፣ የንግድ ይዘት፣ የካምፓኒ ስያሜ ወይም የምርት ስያሜ ጋር ማቀላቀል በደንበኞች ላይ ዉዥንብር ሊፈጥር ስለሚችል ይህንን ላለማድረግ ተስማምተዋል።

የእርስዎ መብቶች

በአዲስባይ ሲገለገሉ ወይም ማንኛዉም አይነት ይዘት ያለውን በድህረ ገጹ ላይ ሲያስቀምጡ ሲያስረክቡ ወይም ሲያሳዩ አዲስባይን ምንም አይነት የባለቤትነት ጥያቄ አያነሣም።ማንኛውም አይነት ይዘት ያለው ነገር እርሶ ወይም የሶስተኛ ወገን ባለቤት፣ ባለቤትነት በድህረገጹ ላይ ሲያስቀምጡ፣ ሲያስረክቡ ወይም ሲያሳዩ የንግድ ምልክቱን፣ የፈጠራ መብትን እና የቅጂና ተዛማጅ መብቶች ባስረከቡት፣ ባስቀመጡት ወይም በሚያሳዩት ይዘት ላይ ሙሉ በሙሉ የማይነካ ሲሆን በተጨማሪም የባለቤትነት መብቱን የማስጠበቅ ሃላፊነት እንደባለቤትነት የርሶ ነው።በአዲስባይ አገልግሎት ድህረገጽ ላይ ያሎትን ይዘት ሲያስቀምጡ ወይም ለአጠቃላይ ህብረተሰብ እንዲታይ በሚያደርጉበት ወቅት ለአዲስባይ አለማቀፋዊነት ውስጥ ያልሆነ ከባለቤትነት መብት ክፍያ ዉጭ ለድጋሚ ጥምረት ፣ ለማሻሻል ፣ ለማተም እንዲሁም እንደዚህ አይነት ይዘትን ማሰራጨት በአዲስ አገልግሎት ላይ ለማሳየት ለማውጣት ለማሰራጨት እና ማስተዋወቅ ለአዲስባይ መብት ሰጥተውታል።አዲስባይ ላይ ይዘቶችን ሲያስቀምጡ ሲያስቀምጡ ሲያስረክቡ በሚያሳዩበት ወቅት ወይም እነዚህን ይዘቶች ከአዲስባይ ማንኛውም አገልግሎት ጋር በማገናኘት ሲያቀርብ የአዲስባይን በህግ የተሰጠው የማስተዋወቅ ወይም የመሸጥ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል። በተጨማሪም አዲስባይ ማንኛዉንም ይዘቶቹን የመቀበል የመከላከል የማስተላለፍ ሙሉ መብቱ የተጠበቀ ነው።

እርሶ ባስረከቡት ይዘት ላይ ሙሉ የሆነ መብት ስልጣን ተጠያቂነት እና ባለቤትነት የተጠበቀ ሲሆን እርስሆም ይህ ንን የመወከልና ዋስትና የማስቀመጥ መብት አለው።

5. ሶፍትዌሮችና ጊዜያዊ ማሻሽያዎች

እርሶ ከአዲስባይ ውጭ የተሰጠን ሶፍትዌሮች በሚጠቀሙበት ወቅት ለእንደዚህ አይነት ሶፍትዋሮች ለመጨረሻ ተጠቃሚ ግለሰብ የተሰጡ የፍቃድ ስምምነቶች እንዲሁም በተቀመጡበት ዉሎች ሆነ በሌላ ዉሎች የመተዳደር ግዴታ አለቦት።የአዲስባይ ሶፍትዌሮች አውቶማቲክካሊ ወዲያዉኑ የሶፍትዌሩን ምህራፍ ቁጥርን ወይም ሌሎች የመለያ ኢንፎርሜሽን በመጠቀም ሪፖርት የሚያደርጉ ሲሆን በተጨማሪም አውቶማቲካሊ ወዲያውኑ የተሻሻለውን ሶፍትዌር በማዉረድ እንዲሻሻል ማድረግ በማስቻል በቀጣይነት የአዲስ ባይ አገልግሎትን እንዲካሄድ የሚያስችል ሲሆን ይኸውም አዲስ የተለቀቁ የሶፍትዌር ምዕራፎችን የተበላሹ የኮምፒውተር ፕሮግራም እንዲሁም ሲስተሞችን መጠገን በትክክል ያልተገለጹ ስተቶችን ይጨምራል።

6. አጠቃላይ ወቅታዊ ተግባሮች ጥቅም እና ማከማቻ

በአዲስ ባይ ግልጋሎት ሲጠቀሙ ለሚፈጠሩ ችግሮች ማለትም ይዘቱን ለማስቀመጥ ሳይችሉ ሲቀሩ በስተት እንዲሁም በድህረ ገጹላይ መተላለፍ ባይችሉ አዲስ ባይ ምንም አይነት ግዴታ እንደሌለበትና ሃላፊነት እንደማይወስድ ተስማምተዋል።በአዲስባይ ለሚያደርጉት የግንኙነት ብዛት ምንም አይነት መረጃ ሲልኩም ሆነ ሲቀበሉ ወይም ባዶ የማከማቻ መጠን እና የብዛት ገደብ ጣሪያ ላያስቀምጥ ይችላል።ነገርግን አዲስባይ የራሱን መብት በመጠበቅ በማንኛውም ወቅት አሳውቆ ወይም ሳያሳውቅ የብዛት ገደብ ጣሪያ ሊያስቀምጥ እንደሚችል ተገንዝበዋል።

7. ለውጦች እና ግልጋሎቶች

አዲስ ባይ በማንኛውም ወቅት እንዲሁም ከጊዜ ወደ ጊዜ የማሻሻል ወይም በጊዜያዊነት ወይም እስከ መጨረሻው አገልግሎቱን አሳውቆም ሆነ ሳያሳውቅ የማቋረጥ መብቱ የተጠበቀ ነው። ስለዚህ አዲስ ባይ አገልግሎቱን በጊዜያዊነትም ሆነ በቀጣይነት በሚያሻሽልበት ወቅት ለእርሶም ወይም ለሌላ ሶስተኛ ወገን ሃላፊነት እንደማይወሰድ ተስማምተዋል።

8. ማቋረጥ

በአዲስባይ መጠቀምሆን በማንኛውም ወቅት ሊያቋርጡ ይችላሉ። አዲስባይም በማንኛውም ወቅት ላይ በምንም ምክንያት ይሁን በአዲስባይ የሚገለገሉበትን አድራሻዎን ሊያቋርጠው ወይም እንዳይንቀሳቀስ ሊያደርግ እንዲሁም ውሉን ሊያቋርጥ እንደሚችል ተስማምተዋል።በዚህ መካከል አዲስ ባይ አድራሻዎን እንዳይንቀሳቀስ ሊያደርግ እንደሚችል እና ምናልባትም የአዲስባይን አገልግሎት ማግኘት በድጋሚ ላያገኙ እንደሚችሉ እንዲሁም አድራሻዎ ወይም አድራሻዎ የተቀመጡ ይዘቶችን ፋይሎች ላያገኝ እንደሚችሉ

9. ማስተዋወቂያዎች

አንዳንድ የአዲስባይ ግልጋሎቶች የሚደገፉት ከማስተዋወቂያ ከሚገኝ ገቢ ስለሆነ ምናልባትም የተለያዩ የማስተዋወቂያዎች በአገልግሎቱ ላይ ይታያሉ እንደዚህ አይነት ማስተዋወቂያዎች አላማ ያደረገው በአዲስባይ ግልጋሎት ላይ የተቀመጡ የኢንፎርሜሽን ይዘቶችን እንዲሁም በአዲስ ባይ ላይ ለሚደረጉ ጥያቄዎች ወይም ሌላ አይነት ኢንፎርሜሽን ነው። በአዲስባይ አገልግሎት ላይ የሚደረጉ ማስተዋወቂያዎች ሁኔታ ስርአት እንዲሁ ሊቀያየሩ ይችላሉ። የእናንተ የአዲስባይ አገልግሎትን ተጠቃሚነት ከግምት በማስገባት እንደዚህ አይነት ማስተዋወቂያዎች በአዲስባይ ላይ በሚቀመጡበት ወቅት ከማስተዋወቂያዎች የተነሳ ወይም ከአስተዋዋቂዎች አካል ጋር በምታደርጉት ስምምነት በሚፈጠር ጥፋት (ኪሳራ) አዲስባይ ምንም አይነት ተጠያቂነትና ሃላፊነት እንደማይወስድ ተስማምተዋል።

10. መረቦች

የአዲስባይ አገልግሎት ወይም የሌላ ሶስተኛ ወገን ከሌሎች world wide web (ዓለምአቀፋዊ የመረጃ መረብ) ጋር ሊቆራኝ ይችላል። አዲስባይ በእንደዚህ አይነቱ ሁኔታ ላይ ምንም አይነት ቁጥጥር መፍጠር አይችልም ስለዚህ በእንደዚህ አይነት ከውጭ ለሚከሰቱ ድህረገጾች የሰጠው ውክልና የሌላ ሲሆን ለሚኖሩ ይዘቶች ማ ስታወቂያዎች፣ ምርቶች፣ ሸቀጦችን ፣ ወይም ሌላ ንብረቶች የሚወስደው ተጠያቂነት እና ሃላፊነት እንደማይኖር ተስማምተዋል። ከዚህም ባሻገር እንደነዚህ አይነት ይዘቶችን ወይም አገልግሎቶችን በተያያዘ በማንም ለሚፈጠር ኪሳራና ጥፋት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አዲስባይ የሚወስደው ሃላፊነትና ተጠያቂነት እንደማይኖር ተስማምተዋል።

11. ካሳ

አዲስ ባይና በስሩ ያሉ ክፍሎችን፣ አጋሮችን ፣ ሃላፊዎችን፣ ወኪሎቹን፣ ሰራተኞችን፣ አስተዋዋቂ ድርጅቶችን፣ አቅራቢዎችን ወይም ሸሪኮቹን(በአጠቃላይ አዲስባይንና ሸሪኮቹን) ለሌላ ሶስተኛ ወገን ፍላጎት የተነሳ ወይም ከአዲስ ባይ ግልጋሎት ጋር በተያያዘ የውል ስምምነቶችን መጣስም ሆነ ሌላ ተያያዥ እርምጃዎችን ከአዲስባይ አገልግሎት ጋር በተያያዘ ይኸውም ማንኛውንም ተጠያቂነት ወይም ከነዚህ ፍላጎትና ጥፋቶች ኪሳራዎች ጋር ተያያዥ የሆኑ ወጭዎች፣ ክሶች፣ ፍርዶችን፣ የፍርድ ቤት ወጭ እና የጠበቃ ክፍያ ጋር ተመሳሳይነት ላላቸው ገደቦች አዲስባይ ላይ ስላለው ፍላጎትም፣ ክስ ወይም እርምጃዎች ዙሪያ የጽሁፍ ማሳሰብያ የሚመለከታቸው ሲሆን እናንተም በአዲስባይ አላማ ላይ ጉዳት በመሆን ለመካስ ተስማምታችዋል።

12. የዋስትና መብት

ከበታች የተገለጹትን ተረድታችሁ ተስማምታችዋል።

 1. የአዲስባይን አገልግሎት በሚጠቀሙበት ወቅት ሃላፊነቱን የእርሶ ብቻ ነው።የአዲስባይ ግልጋሎቶች “እንደተገኘውና” እና ”ባለበት ሁኔታ” መሰረት ማድረግ ሲሆን በከፍተኛ ደረጃ በህግ እንደተፈቀደው አዲስባይንና ሸሪኮቹን የዋስትና መብት ይገልጻሉ እና ማንኛውም ሁኔታ የተገለጸ ወይም አመልካቾችን ጨምሮ ነገር ግን በአመልካች ዋስትና በሽያጭ ወቅት ያለው ይዘትን ሳይወስን ለልዩ አገልግሎት የሚለጠጥ የማይፈርስ፤
 2. አዲስባይ እና ሸሪኮቹ የአዲስባይ አገልግሎት ፍላጎታችሁን ያሟላል፤ የአዲስ ባይ አገልግሎት የማያቋርጥ ጊዜውን የጠበቀ ፣ ዋስትና ያለው ወይም እንከን የሌሽ ነው፤ ከአዲስባይ ግልጋሎቶት የሚገኘው ውጠት አስተማማኝ፤ በአዲስባይ በመጠቀም ከሚያገኙት የምርት፣ አገልግሎት፣ ኢንፎርሜሽን፣ ወይም የሸመቱት ዕቃ ሙሉ በሙሉ እንደገመቱት ይሆናል፤ማንኛውም በሶፍትዌር ላይ የሚፈጠር እክል ያስተካክላል በማለት ምንም አይነት ማረጋገጫ አይሰጡም፤
 3. ማንኛውም የሚወሰዱ ወይም የሚወርዱ ነገሮች አልያም አዲስባይን አገልግሎት በመጠቀም የሚገኝ ነገሮችን በራስዎ ፍቃድና ሃላፊነት ላይ የተመሰረት ሲሆን እርሶም በብቸኝነት ሃላፊነቱን የእርሶ እንደሆነ ተረድተው በኮምፒውተር ላይም ሆነ በሌሎች መሳሪያዎችን እና የመሳሰሉት ጉዳዮች ሃላፊነቱን ይወስዳሉ፤
 4. ምንም አይነት የጽሁፍም ሆነ የቃል ምክርና ኢንፎርሜሽን ከአዲስባይ ወይም ከአዲስባይ አገልግሎት በውል ስምምነቱ ላይ ከተገለጸው በስተቀር ምንም አይነት የጽሁፍም ወይም የቃልና ምክርና ኢንፎርሜሽን አያገኙም።

13. የተጠያቂነት ገደብ

አዲስባይና ሸሪኮቹ ለእርስዎ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ባጋጣሚ ፣ በልዩ ሁኔታ በጊዜው የሚፈጠር ወይንም በቀጣይነት የሚፈጠርን ጥፋትና ሳይገድብ የትርፍ ማጣት (ኪሳራ)፣ ጥቅም፣ በጎ ፍቃድ ወይም ሌላ አይነት ተጨባጭ ያልሆነ ሃብት ላይ ለሚፈጠር ጉዳት (ምንም እንኳን አዲስ ባይ እንደዚህ አይነቱ ጉዳት ሊፈጠር እንደሚችል አስቀድሞ ምክሩን ቢለግስም) በሚከተሉት መንስኤዎች፡I. የአዲስባይን አገልግሎት መጠቀም ካለመቻል፤II. ሸቀጥ የመግዣ ዋጋ ወይም የአገልግሎት ዋጋ ማንኛውም ሸቀጥ የመግዣ ዋጋ ወይም የአገልግሎት ዋጋ ማንኛውም ሸቀጥ መረጃ ወይም ኢንፎርሜሽን በአዲስባይ ሲገዙ ወይም ሲያገኝ መልዕክት ሲቀበሉ ወይም የሂሳብ ዝውውር አዲስባይን በመጠቀም ሲያካሂዱ፤III. ሃላፊነት በማይወሰ ድበት አካሄድ ወይም ስርጭትም ወይም መረጃዎ ሲገደብ፤IV. ማንኛውም ሶስተኛ አካል በአዲስባይ በመጠቀም በሚሰጠው መግለጫ ወይም ሁኔታ፤V. ሌሎች ሸሪኮች ምንም አይነት ተጠያቂነት እንደማይኖራቸው በተገለጸው መሰረት ተረድተው ተስማምተዋል።

14. መወገድ እና መጠን

ህግን መ ሰረት በማድረግ ከተወገዱት ወይም ከተገደቡት ነጥቦች ዉጭ ይህ ስምምነት ምንም አይነት ገደብና ወሰን በማንኛውም ሁኔታ ላይ፣ማረጋገጫ ላይ መብትወይም ተጠያቂነት የ ማ ስቀረት አላማ የሌለው ሲሆን እንዳንድ ህጎች ማረጋገጫዎችን ወይም ይዘ ቶችን ማስወገድ ሲሆን የሚኖሩትም ገደቦችና መወገጃዎች ከግዴሌሽነት የተነሳ የኮንትራት ውል ስምምነት ማቋረጥ ወይም ባጋጣሚ ወይም በርግጠኝነት የሚጠብቅ ጥፋትን ያካትታል።በዚህ መሰረት ከላይ የተቀመጡ ምዕራፍ ፲፪ እና ፲፫ ላይ የተቀመጡት ደንቦች ብቻ ህጋዊ ሆነው የሚሰሩ በመሆኑ በእናንተ ላይ ተግባራዊ ማድረጉ ወይም የኛ ተጠያቂነት በህግ በተፈቀደው ከፍተኛ የወሰን ድርሻ ይኖረዋል።

15. ሶስተኛ ወገን የለም

በውል ስምምነቱ ላይ ከተጠቀሰው ውጭ ሌላ የሶስተኛ ወገን ተጠቃሚ አካል እንደማይኖር ተስማምተዋል።

16. ማሳሰቢያ

አዲስባይ የተለያዩ ማሳሰቢያዎች የሚሰጥ ሲሆን ይኸውም በውል ስምምነት ላይ የሚኖሩ ለውጦች በተመለከተ በኢሜይል በደብዳቤ ወይም በአዲስ ባይ ላይ ያሳዉቃል፡ አዲስባይ በእቃዎች በገዢዎችና በሻጮች መሃከል የሚደረግ ምንም አይነት የባለቤትነት መብት መተላለፍ እንዲሁም ህጋዊ የኮንትራት ዉል ስምምነት ዉስጥ አይሳተፍም።

17. አጠቃላይ ኢንፎርሜሽን

ጥቅል አስተያየት፡ የውል ስምምነቶች (ማንኛውም ደንቦች መርሆዎች ፣ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚደረጉ ማሻሻያዎች እንደ ፕሮግራም ፖሊሲ እና ህግጋትን ጨምሮ) በእርሶ እና በአዲስባይ መካከል የሚኖረውን አጠቃላይ ስምምነቶች የሚሰጡን ሲሆን ስምምነቶቹም የእርሶን በአዲስባይ የአጠቃቀም መተዳደሪያ በመሆን ለአዲስባይ ለመጠቀም በእሶና በአዲስባይ መሃከል እንደ ቅድመ መነሻ በመሆን ያገለግላሉ።ከዚህ ባሻገር ተጨማሪ የሆኑ የውል ስምምነቶችና ይዘቶች ሊቀርብሎት የሚችል ሲሆን ስምምነቶቹም እርሶ ሲጠቀሙ ወይም ሌሎች የአዲስባይን ግልጋሎቶች የአጋር ግልጋሎቶችና የሶስተኛ ወገን ይዘት ወይም የሶስተኛ ወገን ሶፍትዌሮችን በሚገዙበት ወቅት የሚያገለግሉ ይሆናሉ።

የመዳኛ ሕግ መረጣ የውል ስምምነቶችን እንዲሁም በእርሶና በአዲስ ባይ መካከል የሚኖ ር ግንኙነት የሚዳኙት በኢትዮጵያ ህግ መሰረት ሲሆን ሊኖር የሚችለውን የህግ ክፍተትን ከግምት ውስጥ አያስገባም ። እርሶና አዲስ ባይም በኢትዮጵያ ውስጥ በሚኖሩና በህጋዊ አካላት በሚደረጉ የፍርድ ችሎቶች ላይ ጉዳዮቻቹን ይቋጫሉ።

የስምምነት መሻሻልና መቅለልአዲስባይ ምንም እንኳን መብቶቹን ባያስከብር ወይም ህጋዊ በሆነ መንገድ ሳያስገድድ ቢቀር የተቀመጡት የውል ስምምነቶች በምንም ሁኔታ ሊተው አይችሉም ከውል ስምምነቶች መካከል ብቁ በሆነ የችሎት ሂደት ትክክለኛ አለመሆኑ ቢረጋገጥም እንኳን ለሁለቱ አካላቶች ችሎት በተዋዋሉበት ስምምነት መሰረት ፍርድ እንዲሰጥና ቀሪ የሆኑ የውሉ አካሎች እንዲተገበሩ ያስገድዳል።

የወሰን ሁኔታማንኛውም አይነት የመብት ጥያቄ ወይም ከሚወሰዱት እርምጃ መንስሄ ወይም ሙሉ ከአንድ አመት የሞላው መሆን አለበት ወይም ተመሳሳይ እርምጃዎች ሳቢያ የሚመነጭ ጥያቄ ወይም ለዘላለም ይተግበር።

አዲስባይ.